
ኤስኦኤስ የትምህርትና ሁለንተናዊ አቅም ማጎልበት ፕሮጀክት በደብረታቦር ከተማ ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች የእርባታ በጎችን ድጋፍ እየሰጠ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት 402 የእርባታ በጎችን የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለሆኑ 134 የህብረተሰብ ክፍሎች የመነሻ ድጋፍ በመስጠት ላይ ነው፡፡
የበግ ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረሰብ ክፍሎችም በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ድጋፉን ላደረገላቸው ፕሮጀክትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በኤስኦኤስ የትምህርትና ሁለንተናዊ አቅም ማጎልበት ፕሮጀክት የደብረታቦር ከተማ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አሰፋ አለነ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ የተማሪወችን ትምህርት ማቋረጥ ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በፕሮጀክቱ ለታቀፉ ተማሪወች ወላጆችና አሳዳጊወች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በከተመዋ ፕሮጀክቱ ላቀፋቸው 500 ተማሪወች ለምግብ የሚሆን ድጋፍ በየወሩ ለእያንዳንዱ ተማሪ 500 ብር እያገዛ እንደሚገኝ እና በየአመቱ መስከረም ወር ላይ ደግሞ የትምህርት ቁሳቁስ እየደገፈ መሆኑንም ገልፀው ለተማሪወች ለወላጆችና ለአሳዳጊወችም የተለያዩ ስልጠናወችን መስጠቱን ጠቁመዋል፡፡
አቶ አሰፋ እንዳሉት ከዚህ ቀደም በፕሮጀክቱ ለታቀፉ ብዙ የህብረተሰብ ክፍሎች የእርባታ በጎችንና የወተት ላሞችን በመነሻ ድጋፍ መስጠት መቻሉን አውስተው አሁን ደግሞ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ በመበጀት 402 የእርባታ በጎችን በፕሮጀክቱ ለታቀፉ ለ134 የህብረተሰብ ክፍሎች የመነሻ ድጋፍ እየተሰጠ መሆኑን ገልፀው ድጋፉን እየወሰዱ ያሉት ወገኖች ገቢ እያገኙ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲያስተዳድሩና እንዲለወጡ ታስቦ ድጋፉ እየተደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በፊት የእርባታ በጎች ድጋፍ የተደረገላቸው አብዛኛወቹ የህብረተሰብ ክፍሎች በጎቻቸውን ተንከባክበውና በአግባቡ ይዘው በመጠቀማቸው ጥሩ ገቢ ማግኘት መቻላቸውንም ተናግረው አሁን ላይ ድጋፍ እየተደረጋላቸው ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችም ተጠቃሚ ለመሆንና ለመለወጥ በጎቹን በሚፈለገው አግባብ ተንከባክበው መያዝ እንዳለባቸው አስገንዝበው የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቁመው ፕሮጀክቱም አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ እንደሚያደር አቶ አሰፋ ገልፀዋል፡፡
የበግ ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረሰብ ክፍሎችም በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ድጋፉን ላደረገላቸው ፕሮጀክትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ፕሮጀክቱ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገላቸው መሆኑንም ጠቅሰው ባደረገላቸው ድጋፍም ልጆቻቸው ትምህርታቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዲማሩ ማድረግ መቻላቸውንና ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አሁን የተደረገላቸው የእርባታ በጎች ድጋፍም ከእስካሁኑ በበለጠ አግባብ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው የገለጹት አስተያየት ሰጭወቹ በጎቻቸውን በእንክብካቤ ይዘው የተሻለ ገቢ ለማግኘትና ለመለወጥ እንሰራለንም ብለዋል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ/ም
ተጨማሪ መረጃዎችን በሌሎች የሚዲያ አማራጮች ይመልከቱ!
ፌስ-ቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100064645364506
ቴሌግራም ቻናል ፡- https://t.me/dtcommunication
ትዊተር፡- https://twitter.com/debre_tabor_com
ዩቲዩብ፡- https://youtu.be/BktVrGvXms
