ሀገራችን ኢትዮጵያን በመወከል በጃፓን ሀገር ኮቤ ከተማ በአለም ፓራ ኦሎምፒክ ሻምፒዮና ላይ ተወዳድራ የአለም ሪከርድን በመስበር አሸናፊ ለሆናችውና የወርቅ ሜዳሊያ ላስገኘችው አትሌት ያየሽ ጌቴ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር አቀባበል አደረገ፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያን በመወከል በጃፓን ሀገር ኮቤ ከተማ በአለም ፓራ ኦሎምፒክ ሻምፒዮና ላይ ተወዳድራ የአለም ሪከርድን በመስበር አሸናፊ ለሆናችውና የወርቅ ሜዳሊያ ላስገኘችው አትሌት ያየሽ ጌቴ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር አቀባበል አደረገ፡፡

በከተመዋ የታዳጊ ፕሮጀክት ሰልጣኝ የሆነችውና በጃፓን ሀገር ኮቤ ከተማ በተካሄደው የአለም ፓራ ኦሎምፒክ ሻምፒዮና በ1ሽህ 500 ሜትር ተወዳድራ የአለም ሪከርድን በመስበር ለሀገራችን ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘችውን እና ባንዲራችን ክፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረገችውን አትሌት ያየሽ ጌቴን የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና የስፖርት ቤተሰቡ በተገኘበት አቀባበል ተደርጓላታል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ሰሞኑን በጃፓን ሀገር ኮቤ ከተማ በተካሄደው የአለም ፓራ ኦሎምፒክ ሻምፒዮና ላይ በ1ሽህ 500 ሜትር ተወዳድራ የአለም ሪከርድን በመስበር የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘችውን አትሌት ያየሽ ጌቴን የመንግስት የስራ ሀላፊወችና የስፖርት ቤተሰቡ በተገኘበት እውቅናም ሰጥቷል፡፡

በአቀባበሉና በእውቅና ስነ-ስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደሴ መኮንን እንደተናገሩት አትሌት ያየሽ ጌቴ በአለም ስፖርት አደባባይ አሸናፊ በመሆን የሀገራችን ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲታይ በማድረጓ ለህዝባችንና ለሀገራችን ኩራት ያጎናፀፈች መሆኗን ገልፀው ጠንክረን ከሰራን በአካባቢያችን ብዙ ስፖርተኞችን ማፍራት እንደምንችል ያሳየችና የቤት ስራ የሰጠች ናት ብለዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ስፖርቱን ለማሳደግና ስፖርተኞችን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራና ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም ገልፀው በስፖርቱ ዘርፍ እየሰሩ ያሉ አካላት በሚፈለገው አግባብ ስፖርቱን ለማሳደግና ስፖርተኞችን ለማፍራት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ እሸቱ ውለታው እንዳሉት በከተማ አስተዳደሩ ስፖርቱን ለማሳደግና ስፖርተኞችን ለማፍራት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀው በታዳጊ ፕሮጀክት ታቅፋ በመሰልጠን ላይ ያለችው የፓራ ስፖርት ተወዳዳሪዋ አትሌት ያየሽ ጌቴ ውጤታማ መሆኗን ተናግረዋል፡፡

አትሌቷ ሰሞኑን በጃፓን ሀገር ኮቤ ከተማ በተካሄደው የአለም ፓራ ኦሎምፒክ ሻምፒዮና ላይ ሀገሯን በመወከል በ1ሽህ 500 ሜትር ተወዳድራ የአለም ሪከርድን በመስበር ለሀገራችን ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቷንም ገልፀው ከዚህ በፊትም በዱባይና በቱኒዚያ በተካሄዱ ውድድሮች ላይ አሸናፊ መሆኗን ጠቁመው ጠንካራና በቀጣይም ትልቅ ተስፋ የተጣለባት አትሌት መሆኗን ተናግረዋል፡፡

ከአትሌት ያየሽ በተጨማሪ ብቃት ያላቸው ሌሎችም አትሌቶች መኖራቸውን ጠቅሰው ተወዳዳሪና አሸናፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እገዛና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረው በሚፈለገው አግባብ ስፖርተኞችን ለማፍራትና ስፖርቱን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው መላው ህብረተሰብም ስፖርቱን ለማሳደግ እና ህዝብና ሀገርን የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን ለማፋራት የየድርሻውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ እሸቱ ውለታው መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የአትሌት ያየሽ ጌቴ አሰልጣኝ ክንዱ ሲሳይ እንዳለው አትሌቷ ተወዳዳሪና አሸናፊ እንድትሆን ጠንክረው በመስራታቸው በተወዳደሩባቸው ውድድሮች ሁሉ አሸናፊ መሆን መቻላቸውን ገልጾ ከዚህ በላይ ውጤት ለማምጣት ዝግጅታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግሯል፡፡

አቅምና ችሎታ ያላቸው ሌሎችም አትሌቶች መኖራቸውን ጠቅሶ ስፖርተኞችን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት ከተማ አስተዳደሩ ተገቢውን ድጋፍና እገዛ እንዲያደርግም ጠይቋል፡፡

በመጨረሻም አትሌት ያየሽ ጌቴ ላስመዘገበችው ትልቅ ውጤትና ላበረከተችው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እውቅና እና ስጦታ ተበርክቷላታል፡፡

በተያያዘም አትሌት ያየሽ ጌቴ በቀጣይ በፈረንሳይ ሀገር ፓሪስ ከተማ ላይ በሚካሄደው ስፖርታዊ ውድድር ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያን ወክላ እንደምትወዳደር ተገልጿል፡፡

ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓም

ተጨማሪ መረጃዎችን በሌሎች የሚዲያ አማራጮች ይመልከቱ!

ፌስ-ቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100064645364506

ቴሌግራም ቻናል ፡- https://t.me/dtcommunication

ትዊተር፡- https://twitter.com/debre_tabor_com

ዩቲዩብ፡- https://youtu.be/BktVrGvXms

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top