
በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር በመንግስት በጀትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተሰሩ ያሉትን መሰረተ ልማቶች በጊዜ ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡
በዚህ በጀት አመት በመንግስትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ በከተማ አስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉትን የተለያዩ መሰረተ ልማቶች በተያዘላቸው ጊዜና በጥራት ሰርቶ ለማጠናቀቅ ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተገልጿል፡፡
በከተመዋ በተለያዩ አካባቢወች እየተሰሩ ያሉ መሰረተ ልማቶች ያሉበት ሁኔታ በከተማ አስተዳደሩ አስተባባሪወች፣ በሌሎች የስራ ሀላፊወችና በከተማ ምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ምልከታ ተደርጓል፡፡
ምልከታ በተደረገባቸው አካባቢወች በልማት ኮሚቴነት እየሰሩ ያሉ ነዋሪወች እንደተናገሩት በአካባቢያቸው ከዚህ በፊት መሰረተ ልማት ባለመኖሩ ሲቸገሩ መቆየታቸውን አውስተው አሁን መሰረተ ልማት እየተሰራላቸው በመሆኑ ከነበረው ችግር የሚላቅቃቸውና ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የመሰረተ ልማት ስራው የመጓተት ሁኔታ የሚታይበት መሆኑንም ጠቁመው ዝናቡ ከዘነበ የመሰረተ ልማት ስራውን አስቸጋሪ የሚያደርገው በመሆኑና ጉዳቶችም ሊደርሱ ስለሚችሉ እየተሰሩ ያሉት መሰረተ ልማቶች በጊዜ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ በትኩረት ተይዞ እንዲሰራም ጠይቀዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ ምክር ቤት ዋና-አፈ ጉባኤ ቄስ መልካሙ ላቀው እንደተናገሩት በከተማ አስተዳደሩ መሰረተ ልማቶች በተሻለ አግባብ እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመው የመሰረተ ልማቶቹ በጥሩ ሁኔታ እንዲሰሩና በጊዜ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የመሰረተ ልማቶቹ በተገቢው ሁኔታ እንዲሰሩ ለማድረግ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን እና ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረው ለመሰረተ ልማቶቹ መስሪያ ግብአት በበቂ ሁኔታ እንዲቀርቡ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንደሚገባም አስገንዝበው መሰረተ ልማቶቹን በጊዜ ለማጠናቀቅም ርብርብ ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደሴ መኮንን እንደገለጹት ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ በከተማ አስተዳደሩ መሰረተ ልማቶች በጥሩ ሁኔታ እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመው ቀን ከሌት በመስራት መሰረተ ልማቶችን ከዚህ በላይ በሆነ መልኩ ማስኬድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
መሰረተ ልማቶች በተገቢው ሁኔታ እንዲሰሩ ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረው የሚመለከታቸው አካላትም መሰረተ ልማቶቹ በጥሩ መንገድ እንዲሰሩ ለማድረግ በትኩረት ይዘው እንዲሰሩ አሳስበው ተባብረንና ተጋግዘን በመስራት መሰረተ ልማቶችን በሚፈለገው አግባብ ማስኬድ አለብንም ብለዋል፡፡
ለመሰረተ ልማቶቹ መስሪያ የሚሆኑ ግብአቶች በአግባቡ እንዲቀርቡ ለማድረግ እንደሚሰራ የገለጹት ከንቲባው ሁኔታወችን በማመቻቸት መሰረተ ልማቶችን በጊዜ ለማጠናቀቅ መስራት እንደሚገባም አስገንዝበው ህብረተሰቡ የሚሰሩ መሰረተ ልማቶችን በባለቤትነት ይዞ ሊጠቀም ይገባልም ብለዋል፡፡
በተያያዘም በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር በመንግስት በጀትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ የጠጠር መንገዶች፣ የውሀ ማፋሰሻወች፣ የመንገድ ከፈታወች፣ የኮብል ስቶን መንገዶችና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች እየተሰሩ መሆናቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ/ም
ለተጨማሪ መረጃዎችን በሌሎች የሚዲያ አማራጮች ይመልከቱ!
ፌስ-ቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100064645364506
ቴሌግራም ቻናል ፡- https://t.me/dtcommunication
ትዊተር፡- https://twitter.com/debre_tabor_com
ዩቲዩብ፡- https://youtu.be/BktVrGvXms
