የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተልእኮ ለማስፈፀም እየሰራ ያለው ጽንፈኛ ሀይል በፀጥታ አካሉ ሽንፈትን ተከናንቦ መመለሱ ተገለፀ፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ መምሪያ ከተቋሙ ሰራተኞች እና ከሰላም አስከባሪዎች ጋር የግዳጅ አፈጻፀም ግምገማ እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአብክመ ሚሊሻ ቢሮ ሀላፊ ልዩ አማካሪ ኮምሽነር አዲሴ እንግደው እንደተናገሩት ጠላት ደብረታቦርን በመያዝ አስከፊ ድርጊቶችን ለመፈፀም ቢመጣም የፀጥታ ሀይሉ ባደረገው ተጋድሎ የጠላት ህልም ሳይሳካ መቅረቱን ገልፀው በዚህም ክልሉን ከመፍረስ ማዳን ተችሏል ብለዋል፡፡
ሰላምን ለማረጋገጥ ተግባራትን በሚፈለገው መንገድ መፈፀም እንደሚገባ እና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበው የፀጥታ አካሉ ስነልቦናውን ከፍ ማድረግ እና ሁለንተናዊ ዝግጅት ማድረግ እንዳለበትም ጠቁመው በየደረጃው ካለው የፀጥታ ሀይል ጋር በቅንጅት መስራት ይገባልም ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ መምሪያ ሀላፊ አቶ ብሩክ አለምነው እንደገለጹት የጠላት እሳቤ መንጋውን በማብዛት ካለምንም መስዋትነት ከተመዋን መቆጣጠር እና ህዝቡን ማንገላታት እንደነበር አንስተው የፀጥታ አካሉ ባሳየው ቁርጠኝነት እና ባደረገው ተጋድሎ የጠላት ሀይል አፍሮ መመለሱን ተናግረዋል፡፡
ጽንፈኛ ሀይሉ በታሪካዊ ጠላቶቻችን የተለያየ ድጋፍ የሚደረግለት መሆኑንም ጠቅሰው በተደረገው ጦርነት ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጭምር ሽንፈት መከናነባቸውን ጠቁመው ያለውን የጠላት ሴል በአግባቡ መለየት፣ ሰርጎ ገብን መከታተል፣ ራስን ማጥራት፣ ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር፣ ስነልቦናን መገንባትና ሚስጢር መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
የደብረታበር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አብራራው አበጀ በበኩላቸው የጠላት ሀይል ከተመዋን ለማውደም እና ህዝቡን ለማንገላታት በርካታ ወራሪውን ይዞ ቢመጣም የፀጥታ አካሉ በጀግንነትና በቁርጠኝነት ትግል አድርጎ የጠላት ሀይልን አንገት አስደፍቶ መመለሱን አንስተው ለቀጣይ ተልእኮ እና ግዳጅ ዝግጁ መሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ህዝቡ መረጃ በመስጠት ትልቅ እገዛ ማድረጉን እና መረጃን በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግም ተናግረው ያሉትን ጥንካሬዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እና ክፍተቶችን ደግሞ ማስተካከል እንደሚገባ አስገንዝበው የደንብ ልብስን በአግባቡ መጠቀም እና ስራዎችን በቅንጅት መስራት አለብንም ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የደብረታቦር ከተማ አስተዳደርን እና የደቡብ ጎንደርን ሰላምና ፀጥታ እያስተባበሩ ያሉት ኮሎኔል አለም እንደተናገሩት ክልሉን ለማፍረስ ያልተሴረ ሴራ እና ያልተደረገ ነገር እንደሌለ አንስተው አሉባልታንና ትክክለኛ ያልሆነ መረጃን ወደ ጎን በመተው የጠራ አስተሳሰብን ይዞ ተግባራትን በአግባቡ መፈፀም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የፀጥታ አካሉ ወደ ደብረታቦር የመጣውን የጠላት ሀይል አሳፍሮ መመለሱ ይበል የሚያስብል መሆኑን አንስተው ሰላምን ለማረጋገጥ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ መስራት እንደሚገባም አስገንዝበው የስነልቦና ዝግጅት ማድረግ እና ሰርጎ ገቦችን መከታተል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተሳተፉ አካላትም በሰጡት ሀሳብ በርካታ የጠላት ሀይል ከተመዋን ለማውደም እና ህዝቡን ለማበሳቆል ቢመጣም በመላው የፀጥታ ሀይል ቁርጠኝነትና ቅንጅት ተመትቶ መመለሱን ተናግረው በቀጣይም ጠላትን ለማሳፈር ሁለንተናዊ ዝግጅት ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡
በጠላት ሀይል የተያዙትን የደቡብ ጎንደር ወረዳዎችና ከተሞች ለማስለቀቅም ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አንስተው የደብረታቦር ከተማ አስተዳደርን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ ከደቡብ ጎንደር ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው የሚሰጣቸውን ተልእኮና ግዳጅ ለመፈፀምም ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ/ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top