የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኢንቨስትመንቱን ለማነቃቃት ከኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ንቅናቄ ጋር አያይዞ የተለያዩ ሁነቶችን አካሂዷል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሀላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፣ የተለያዩ አደረጃጀት ተወካዮች የተገኙ ሲህን የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ አስራት መሰለ እንደተናገሩት በከተመዋ የተቀዛቀዘውን ኢንቨስትመንት ለማነቃቃት በትኩረት ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አንስተው በዛሬው እለት የተካሄዱት ሁነቶች እና በነገው እለት የሚካሄዱት ፕሮግራሞችም ኢንቨስትመንቱ ላይ መነቃቃትን ለመፍጠር መሆኑን ገልፀው ከተመዋን ለማልማትና ለማሳደግ ሁላችንም መስራት አለብን ብለዋል፡፡
ማህበረሰቡ በተለያየ መንገድ ኢንቨስትመንቱን እያገዘና እየደገፈ መሆኑንም አንስተው ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ግንባታቸውን አቁመው የነበሩ ባለሀብቶች ወደ ስራ እንዲገቡ እና ማምረት አቁመው የነበሩት ፕሮጀክቶች ወደ ማምረት እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመው በርካታ ባለሀብቶች በከተመዋ እየሰሩ መሆናቸውን እና ሌሎችም ባለሀብቶች መጥተው ኢንቨስት ኢንዲያደርጉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ ከተሳተፉ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት መካከል አቶ ደሳለኝ ሲራክና ሀምሳ አለቃ ዮንስ ታደሰ በሰጡት አስተያየት ከተመዋ ባላት አቅም ልክ ኢንቨስትመንቱን በአግባቡ ለማስኬድ በቅንጅትና በትብብር መስራት እንደሚገባ አንስተው የተቀዛቀዘውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማነቃቃት የተካሄዱት ሁነቶች ጥሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በከተመዋ በአሁኑ ጊዜ የተሻለ ሰላም በመኖሩ የኢንቨስትመንት ስራውን በጥሩ መንገድ ለማስኬድ ምቹ በመሆኑ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ባለሀብቶች ወደ ከተመዋ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ኢንቨስትመንቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎችም በሰጡት ሀሳብ ማህበረሰቡ ከተመዋን የሚመጥን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሰሴ እንዲኖር ፍላጎት ያለው መሆኑን አንስተው የኢንቨስትመንቱ እንቅስቃሴ እንዲጠናከር ለማድረግ በተለያየ መንገድ እያገዙ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የተቀዛቀዘውን ኢንቨስትመንት ለማነቃቃት እንደነዚህ አይነት ሁነቶች ትልቅ ፋይዳ ያላቸው በመሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ተናግረው ከተመዋ ላይ የተሻለ ሰላም ያለ በመሆኑ ባለሀብቶች በኢንቨስትመንቱ ሊሳተፉ እንደሚገባ ጠቁመው ከተማችን ለማልማት በጋራ መስራት አለብንም ብለዋል፡፡
በደብረታቦር ከተማ ከኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ንቅናቄ ጋር ተያይዞ የጎዳና ላይ ሩጫ፣ የገመድ ጉተታ ውድድር እና ሌሎችም ሁነቶች የተካሄዱ ሲሆን በነገው እለትም የተለያዩ ፕሮግራሞች ይካሄዳል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ጥር 23 ቀን 2018 ዓ/ም
