በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተመላከተ፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከመምሪያና ከተጠሪ ጽ/ቤት የስራ ሀላፊዎች፣ ከክፍለ ከተማ አስተባባሪዎችና ከሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ጋር የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን የ2018 በጀት አመት የስድስት ወራት እቅድ አፈጻፀም ግምገማ መድረክ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ እንዳልካቸው ዳምጠው በመጀመሪያው መንፈቅ አመት በፓርቲ የተከናዎኑትን ተግባራት ሪፖርት ቀረቡ ሲሆን በፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት፣ በአደረጃጀት፣ በፓርቲ ፋይናስና በሌሎችም ዘርፎች የተሰሩትን ስራዎች አመላክተዋል፡፡ የፓርቲው ኢንሸቲቭ ስራዎችም በጥሩ መንገድ እየተሰሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
ከበርካታ የህብረተሰብ ክፍል ጋር ተደጋጋሚ መድረኮችን በማስኬድ በወቅታዊ የሰላምና የልማት ጉዳዮች እንዲሁም በሀገራዊና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት መካሄዱን ገልፀው ህዝቡ ነባራዊ ሁኔታውን እየተረዳ በመምጣቱ ሰላምን ለማምጣት እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች እያገዘ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡ በቀጣይም ተግባራትን ከእስካሁኑ በበለጠ ሁኔታ ለማከናዎን በትኩረት ይዘን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ደበበ አክሎግ እንደተናገሩት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች በሚፈለገው መንገድ እንዲከናዎኑ ለማድረግ አመራሩ በትኩረት ይዞ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበው ተግባራትን ከአሁኑ በተሻለ አግባብ መፈፀም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ለዜጎች በአግባቡ የስራ እድሎችን ለመፍጠር እና ገቢን በተገቢው ሁኔታ ለመሰብሰብ ሁሉም በባለቤትነት ይዞ መስራት እንዳለበት እንዲሁም የፓርቲ ኢንሼቲቭ የሆኑ ተግባራትን በጊዜ የለኝም ስሜት ማከናዎን እንደሚገባ አስገንዝበው ስራዎቻችን በተነሳሽነት መስራት አለብን ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን እንደገለጹት በአንዳንድ ተቋማት የተከናዎኑት ስራዎች ይበል የሚያሰኙ መሆናቸውን እና በአንዳንዶቹ ደግሞ የሚቀር ነገር ያለ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ስራዎችን በአግባቡ ለመፈፀም በትኩረት ይዞ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
አመራሩ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትና ተልዕኮዎችን በአግባቡ በመረዳትና በመፈጸም ውጤታማ ስራ መስራት ይገባልም ብለዋል፡፡
በመድረኩ በስድስት ወራት በፓርቲ ተግባራት የተሻለ አፈጻጸም ላሳየ ክፍለ ከተማ፣ወጣት ክንፍና ሴቶች ክንፍ አደረጃጀቶች የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ጥር 16 ቀን 2018 ዓ/ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top