የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም
በደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የፅንፈኛው ቡድን አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የሠላም ጥሪውን ተቀብለው ገብተዋል።

የሰላም ጥሪውን ተቀብለው የመጡ ታጣቂዎችን የ10ኛ ዕዝ ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አሰጋ አከለና የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ቢሮ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መንበረ ክፈተው የሀይማኖት አባቶችና የወረዳው አመራሮች ተቀብለዋቸዋል።
ሌተናል ኮሎኔል አሰጋ አከለ ለሰራዊታችን እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ የሰጡ የቡድኑ አባላት ስህተታቸው ገብቷቸው ህዝባቸውን ይቅርታ ጠይቀው በመመለስ ነገ ከመንግስት ጎን ሆነው ሀገራቸውን ለማገልገል መወሰናቸው ተገቢ ነው ብለዋል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ቢሮ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መንበረ ክፈተው በዞኑ ግዳጅ እየተወጣ ያለው መከላከያ ሠራዊት የሚያደርገው ተደጋጋሚ ስምሪት እና የተደረጉ ውይይቶች በሠላም እንዲገቡ ማገዙን ገልፀዋል። ዘጋቢ ብርሃኑ አባተ ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
