የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያውን ግማሽ አመት እቅድ አፈጻፀም በመገምገም የቀጣይ ስምሪት ሰጥቷል፡፡


በመድረኩ ላይ የመክፈቻ
ንግግር ያደረጉት የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን እንዳሉት ሴቶች የተሳተፉባቸው ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን እና በአንጻሩ የሴቶች ተሳትፎ አናሳ በሆነባቸው ስራዎች ላይ ውጤት እንደማይገኝ አንስተው ሴቶች እያደረጉት ያለውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና እየሰሯቸው ያሉትን ስራዎች አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ሴቶችን በማብቃት የመሪነት ሚናቸውን ለማሳደግ በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚገባም ጠቁመው ሴቶች በየደረጃው ባለው የመሪነት ቦታ ላይ ለመስራት ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው አስገንዝበው ከሴቶች አኳያ የሚሰሩትን ስራዎች በአግባቡ ለማስኬድ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባልም ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሀላፊ ወ/ሮ ቤተልሄም ክበቤ በመጀመሪያው ግማሽ አመት የተከናዎኑትን ተግባራት እቅድ አፈጻፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ሴቶች በክረምቱ እና በበጋ ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መስራታቸውን ገልፀዋል፡፡ ሴቶች በቤተሰብና በህብረት እንዲወያዩ መደረጉን፣ በሌማት ቱርፋት ስራዎች ላይ ተሰማርተው ተጠቃሚ እንዲሆን መደረጉን፣ የሴቶችን አቅም ለመገንባት መሰራቱን፣ አዲስ አባላትን ለማፍራት መሰራቱን፣ ሴቶች የአባልነት ክፍያ እንዲከፍሉ መደረጉን እና ሌሎችም ተግባራት መከናዎናቸውን አንስተዋል፡፡
ሀላፊዋ በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎችንም ያቀረቡ ሲሆን የሴቶችን አደረጃጀት ማጠናከር፣ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ፣ ቀጣዩ ምርጫ የተሳካ እንዲሆን በትኩረት መስራት፣ የቤተሰብና የህብረት ውይይቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እና ሌሎችም ተግባራት እንደሚከናዎኑ ጠቅሰው ስራዎቻችን ተቀናጅተንና ተባብረን መፈፀም አለብንም ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙ አካላትም በሰጡት ሀሳብ ሴቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፉ እና በርካታ ስራዎችን እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀው ከሴቶች አኳያ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መስራታቸውን እና ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመው ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና ክፍተቶችን ለማስተካከል እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ሴቶች በተለያየ መንገድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አንስተው የሴቶችን አደረጃጀት አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ቀጣዩ ምርጫ በአግባቡ እንዲካሄድ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለንም ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ያየሽ ድረስ እንደገለጹት ሴቶች በተለያየ አግባብ ተሳትፎ እያደረጉ በመሆናቸው ሁለንተናዊ ተሳትፏቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበው የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁላችንም ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የሴቶችን አደረጃጀት አጠናክሮ በማስቀጠል ተግባራትን በሚፈለገው መንገድ ለመፈፀም በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚገባም ጠቁመው ስራዎችን በጥሩ መንገድ ለመስራት ተጋግዘንና ተባብረን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ውባለም ታረቀኝ እንደተናገሩት ሴቶች ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰሩ መሆናቸውን እና አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸው አንስተው ተሳትፏቸውንና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ጠንክረው ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የሴቶችን የመሪነት ሚና ለማሳደግ፣ አደረጃጀቶችን ለማጠናከር እና ለሴቶች የስራ እድሎችን ለመፍጠር እንዲሁም በሌማት ቱርፋት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበው ቀጣዩ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ እንዲካሄድ ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ጥር 14 ቀን 2018 ዓ/ም
