የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የ2018 በጀት አመት የስድስት ወራት እቅድ አፈጸፀም ግምገማ መድረክ አካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ የመምሪያው እቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ኦፊሰር አቶ አዳነ አለምነው የተቋሙን የ2018 በጀት አመት የመጀመሪው ስድስት ወር እቅድ አፈጻፀም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
በእናቶችና ህጻናት ጤና፣ በስርአተ ምግብ፣ በተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥርና ክትትል፣ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ቁጥጥርና ክትትል፣ በሀይጅንና ሳኒቴሽን፣ በጤና እና ጤና ነክ፣ በጤና መድን፣ በወጣቶችና ስነተዋልዶ፣ በማህፀን ጫፍ ካንሰር ልየታና ህክምና እንዲሁም በሌሎችም ተግባራት ላይ ያሉትን አፈጻፀሞች አመላክተዋል፡፡
የጤና መድን ተግባርን ከ100 ፐርሰንት በላይ ማሳካት መቻሉን እና ሶስት ቀበሌዎችን ሞዴል ማድረግ መቻሉንም ገልፀው በአብዛኛው ተግባራት ላይ የተሻለ አፈጻፀም መኖሩን አንስተው ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና ክፍተቶችን ደግሞ ለማስተካከል በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበው ስራዎቻችን ውጤታማ ለማድረግ ተቀናጅተንና ተጋግዘን መስራት አለብንም ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተሳተፉ አካላትም በሰጡት ሀሳብ ተግባሮቻቸውን በተገቢው ሁኔታ ለመፈፀም ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን እና አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀው ቀበሌዎቻቸውን ሞዴል ለማድረግ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ጠቁመው ጥንካሬዎችን እንደሚያስቀጥሉ እና ክፍተቶችን ደግሞ እንደሚሞሉ ተናግረዋል፡፡
የነፍሰ ጡር እናቶችን ክትትል በሶስቱም ጤና ጣቢያዎች በማስኬድ በሆስፒታሉ ላይ የሚፈጠረውን ጫና መቀነስ እንደሚያስፈልግ አንስተው ከጤና ጣቢያዎች ወደ ሆስፒታሉ የሚደረገውን የሪፈር ቅብብሎሽ ለማሳለጥ በአግባቡ መስራት አለብንም ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ማርየ እንግዳየሁ እንደገለጹት በባለፈው በጀት አመት ተግባራትን በጥሩ መንገድ ለመፈፀም የተቻለበት ሁኔታ መኖሩን አስታውሰው በተያዘው በጀት አመትም ተግባራትን በተሻለ ሁኔታ ለማከናዎን ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበው በመጀመሪያው ስድስት ወራት የተሰሩት አብዛኛዎቹ ስራዎች ጥሩ መሆናቸው ጠቅሰው ጥሩ አፈጻፀም ያላቸውን ለማስቀጠል እና ዝቅ ያሉትን ደግሞ ለማስተካከል ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
በተቋሙ የሚሰሩትን እና በጤና ተቋማት የሚፈፀሙትን ተግባራት በሚፈለገው መንገድ ለማስኬድ በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚገባም አስገንዝበው በአመራሩና በባለሙያው ርብርብ የጤና መድን አፈጻፀም ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ጠቁመው ስራዎቻችን ውጤታማ ለማድረግ ተጋግዘንና ተባብረን መስራት አለብንም ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ በረከት ገደፋው እንደተናገሩት በጤና ዘርፉ የ2018 በጀት አመት ስድስት ወራት አፈጻፀም የተሻለ መሆኑን አንስተው ከሚፈለገው አፈጻፀም አኳያ የሚቀር ነገር ያለ በመሆኑ ተግባራትን በሚፈለገው መንገድ ለመፈፀም በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበው ስራዎቻችን ውጤታማ እንዲሆኑ የየበኩላችን ድርሻ መወጣት አለብን ብለዋል፡፡
በተሰራው ስራ የጤና መድን ተግባር ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን አንስተው በጤና ጣቢያ ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአግባቡ ለመስጠት እና ቀበሌዎችን ሞዴል ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም አስገንዝበው የኤችአይቪ ምርመራን ማሳደግ እና የግንዛቤ ፈጠራ ስራን በተገቢው ሁኔታ መስራት እንዲሁም የህጻናትንና የእናቶችን ጤና መጠበቅ አለብን ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ በግማሽ አመቱ የተሻለ አፈጻፀም ላላቸው ጤና ጣቢያዎች እና ቀበሌዎች ጤና መምሪያው እውቅና ሰጥቷል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ጥር 08 ቀን 2018 ዓ/ም
