የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ በከተመዋ በቀጣይ የሚካሄደውን “የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” ንቅናቄ በጥሩ መንገድ ለማስኬድ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

በመድረኩ ላይ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ አስራት መሰለ በከተመዋ የሚካሄደውን ንቅናቄ ውጤታማ ለማድረግ የሚከናዎኑ ተግባራትን የያዘ ማስፈፀሚያ ሰነድ አቅርበዋል፡፡ ከተመዋ ለኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፉ ምቹ ሁኔታዎች ያሏት መሆኑን እና በርካታ አማራጮች መኖራቸውን ገልፀው ዘርፉን በተሻለ መንገድ ለማስኬድ ሁላችንም በባለቤትነት ይዘን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
በከተመዋ የሚካሄደው “የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” ንቅናቄ የተሰሩትን ስራዎች በማሳየት ባለሀብቶች መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ፣ በከተመዋ ያሉትን ኢንቨስትመንቶች ለማጠናከር፣ የተሻለ ሰላም መኖሩን በማሳየት ባለሀብቶች ወደ ስራ እንዲገቡ እና የተቀዛቀዘውን ኢንቨስትመንት ለማነቃቃት መሆኑን ጠቅሰው ንቅናቄውን የተሳካ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን እና ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀው ወደ ከተመዋ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና እንዲነቃቃ ለማድረግ በትኩረት ይዘን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙ አካላትም በሰጡት ሀሳብ በከተመዋ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እና ባለሀብቶችን ለመሳብ ሁሉም አካል በባለቤትነት ይዞ መስራት እንዳለበት አንስተው ኢንቨስትመንቱን በጥሩ መንገድ ለማስኬድ እና ዘርፉን ለማነቃቃት ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
መሬት ለኢንቨስትመንት ወስደው ለብዙ አመታት አጥረው ያስቀመጡ ባለሀብቶች ወደ ስራ እንዲገቡ ግፊት ማድረግ እንደሚያስፈልግ እና ወደ ስራ በማይገቡት ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ተናግረው ሰላሙንና ፀጥታውን አስተማማኝ ለማድረግ በትኩረት መሰራት እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡
በመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱት የተለያዩ ሀሳቦችም የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ አስራት መሰለ መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን እንዳሉት “የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” ንቅናቄን በከተማችን በተሻለ መንገድ ለማስኬድ እየተሰሩ ያሉት ስራዎች ጥሩ መሆናቸውን እና አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረው የንቅናቄውን አላማ ለማሳካት በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በከተመዋ የተሻለ ሰላም በመኖሩ የተለያዩ ስራዎችን ካለ ስጋት መስራት የተቻለበት ሁኔታ መኖሩን አንስተው ኢንቨስትመንት ለማድረግም የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታ ያለ በመሆኑ ኢንቨስትመንቱን በአግባቡ ለማስኬድ እና የልማት ስራዎችንም አጠናክሮ ለማስቀጠል በጋራ መስራት አለብን ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደሴ መኮንን እንደተናገሩት የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፉ በሀገራችን የሚደረገውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ለማሳካት ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልፀው ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
በከተማችን የሚካሄደው “የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” ንቅናቄ የተቀዛቀዘውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማነቃቃት የሚያስችል መሆኑን አንስተው ያለውን ኢንቨስትመንት አጠናክሮ ማስቀጠል እና ሌሎች ባለሀብቶች ወደ ከተመዋ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ በትኩረት ይዘን ልንሰራ ይገባልም ብለዋል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ጥር 07 ቀን 2018 ዓ/ም
