የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የብዙ ታቦታት መውረጃ የሆነው የአጅባር ሜዳ በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት ፅዳት ተካሂዷል።

በፅዳት ዘመቻው የተገኙት የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሃይለኢየሱስ ሶሎሞን እንዳሉት ጥምቀትን በአጅባር ሜዳ ብዙ ምእመን እና ካህናት የሚታደሙበት መሆኑን አውስተው ለዚህም ወጣቶች ክብር ሰጥተው ፅዳት ማካሄዳቸው ታላቅነት ነው ብለዋል።
ምክትል ከንቲባው ከፅዳት ባለፈ የከተማችን በጎ ፈቃደኛ ወጣቶ የክረምትና በጋ በጎ ተግባሮችን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ተናግረው ከፊታችን የሚከበረውን የመርቆሪዎስን በአል በስኬታማነት ለማክበር ወጣቶች ትልቅ ድርሻ እንዳለባቸው እና ትኩረት በማድረግ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል።
በፅዳት ዘመቻውም የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀይለኢየሱስ ሶሎሞን፣ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ኋላፊ አቶ ሀብታሙ ጌታሁን ፣ የደብረታቦር ከተማ ወጣት ክንፍ ኋላፊ አቶ መለሰ አለሙ እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ጥር 8/2018 ዓ.ም
