በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ጎንደር ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ተወካይ ሀለፊ አቶ ገደፋው ወርቁ እንዳሉት ዞናችን የበርካታ ባህላዊ፣ታሪካዊ እና ሀይማኖታዊ ቅርሶች ባለቤት ነው ብለዋል።

የውድድርሩ አላማም በዞናችንና በከተማው ያሉ ባህሎቻችን እሴታቸውን ጠብቀው እንዲሄዱ እና አሸናፊዎቹም ዞኑን ወክለው በክልል ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው ብለዋል።
ኪነ ጥበብ ወኔን በመቀስቀስና በማጀገን ሀገርን ለማጽናት መነሳሳትን ለመፍጠር ትልቅ አቅም እንዳለውም ገልጸዋል።
ዞናችን በርካታ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ያፈራች መሆኗን ገልጸው ተወዳዳሪዎቹም ኪነ ጥበብን ባግባቡ ወዶና ተንከባክቦ በመያዝ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ መጣር እንዳለባቸው አቶ ገደፋው አስገንዝበዋል።
በፌስቲቫሉም በዞኑ ያሉ 12 ወረዳዎች በባህል ሙዚቃና በቲያተር እንደሚወዳደሩ እና ለከታታይ ሁለት ቀን እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 08/2018 አ.ም
