
አላግባብ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ህገ-ወጥ የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወሰደ።
በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር የዶላር ምንዛሬ ጭምሯል በሚል ምክኒያት አላግባብ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉና ምርት በደበቁ ህገ-ወጥ የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ የእርምት እርምጃ መውሰዱን የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ተጠሪ ፅ/ቤት ኃላፊና ተወካይ ከንቲባ አቶ ክብረት ተስፋየ ገልፀዋል።
አግባብ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የተደረገባቸው መሰረታዊ ምርቶች ዘይት 950 ብር የነበረውን 1200 ብር ፣ሰኳር 115 ብር የነበረውን 125 ብር፣ ጤፍ 9 ሽህ ብር የነበረውን እስከ 13 ሽህ ብር እና የተለያዩ ማንኛውም ሸቀጣ ሸቀጥ ጭማሪ ያደረጉ ነጋዴዎች እና ድርጅቶች ላይ የእርምት እርመጃ ተወስዷል ብለዋል።
ህግና መመሪያን አክብረው በማይሰሩ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ የተጀመረውን ህግ የማስከበር ሥራ ከዚህ የበለጠ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ያሉት አቶ ክብረት ተስፋየ ምርት የሚያሸሹ፣ የሚደብቁና አላግባብ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን በማጋለጥና ለንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ጥቆማ በመስጠት ማህበረሰባችን የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ሀምሌ 30/2016 አ/ም
ለተጨማሪ መረጃዎችን በሌሎች የሚዲያ አማራጮች ይመልከቱ!
ፌስ-ቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100064645364506
ቴሌግራም ቻናል ፡- https://t.me/dtcommunication
ትዊተር፡- https://twitter.com/debre_tabor_com
ዩቲዩብ፡- https://youtu.be/BktVrGvXms
