ጠላት የፈፀመው እኩይ ድርጊት ህዝብን የሚጎዳ በመሆኑ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር መንግስት ሰራተኞች አወገዙ፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከመንግስት ሰራተኛው ጋር በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡
በመድረኩ ላይ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሀብታሙ ጌታሁን ወቅታዊ ሁኔታውን አስመልክተው ሰነድ አቅርበዋል፡፡ ጠላት ደብረታቦርን በመያዝ የሚፈልገውን ድርጊት ለመፈፀም ቢመጣም በአመራሩ ቁርጠኝነት እና በሁሉም የፀጥታ ሀይል ተጋድሎ የጠላት ሀይል ትልቅ ኪሳራ ደርሶበት እና ተመትቶ መመለሱን ገልፀዋል፡፡ የከተመዋ ህዝብ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖችም በተለያየ መንገድ እገዛ ማድረጋቸውን አንስተዋል ለጠላት የሚላላኩ አንዳንድ ግለሰቦች ያሉ በመሆናቸው ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ወደ ከተመዋ መጥቶ የነበረው ወራሪ ሀይል የውጭ ጠላቶች ያደርጉታል ተብሎ በማይታሰብ ደረጃ እኩይ ድርጊት መፈፀሙን ተናግረው ህጻናትንና ሴቶችን መድፈሩን፣ በመንግስት ተቋማት ሀብት ንብረት እና በግለሰብ ቤት ሀብት ንብረት ውድመትና ዘረፋ መፈፀሙንም ገልፀው ጉዳቱ የጋራ በመሆኑ ሁላችንም የጋራ አቋም ይዘን ማውገዝና ይበቃል ማለት አለብን ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተሳተፉ መንግስት ሰራተኞችም በሰጡት ሀሳብ የጠላት ሀይል ከተመዋን ለማውደም እና ህዝቡን ለማበሳቆል ቢመጣም በአመራሩ ቁርጠኝነት እና በመላው የፀጥታ አካል ተጋድሎ ተመትቶ መመለሱ ይበል የሚያስብል መሆኑን ተናግረው ለአመራሩና ለፀጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ወራሪ ሀይሉ የውጭ ጠላቶች ያደርጉታል በማይባል ሁኔታ ጉዳት ማድረሱን አንስተው በተፈፀመው እኩይ ድርጊት ማዘናቸውን የገለጹ ሲሆን ድርጊቱ ህዝቡን የሚጎዳ በመሆኑ አውግዘው የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመስራት መተባበር እንደሚያስፈልግ ጠቁመው የፀጥታ አካሉን ማጠናከር እና በቅንጅት መስራት ይገባልም ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ደበበ አክሎግ እንደገለጹት ወደ ከተመዋ የመጣው የጠላት ሀይል በአመራሩ ቁርጠኝነት እና በፀጥታ አካሉ ተጋድሎ ተመትቶ መመለሱን አንስተው ህዝቡም ከመንግስት ጎን ሁኖ በተለያየ መንገድ ማገዙን ተናግረው ለመላው የፀጥታ አካል እና ለህዝቡ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የጠላት ሀይል በያዛቸው አካባቢዎች በርካታ እኩይ ድርጊቶችን እየፈፀመ መሆኑንም ጠቅሰው በደብረታቦር ከተማም በቆየበት አጭር ጊዜ ህጻናትንና ሴቶችን መድፈሩን፣ የመንግስትና የግለሰብ ሀብት ንብረት ማውደሙን እና መዝረፉን ገልፀው ይህ ሀይል በከተመዋ ቢውል ቢያድር ምን እንደሚያደርግ ማሳያ በመሆኑ ሁላችንም ማውገዝ አለብን ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደሴ መኮንን እንደተናገሩት የጠላት ሀይል በመንግስት ተቋማት ሀብት ንብረት እና በግለሰብ ቤት ሀብት ንብረት ውድመትና ዘረፋ ቢፈጽምም በነበረው የአመራሩ ቁርጠኝነት እና የፀጥታ አካሉ ተጋድሎ ተመትቶ መመለሱን አንስተው ህዝቡም ከመንግስት ጎን ሁኖ በተለያየ አግባብ እገዛ በማድረጉ አመስግነዋል፡፡
ወራሪ ሀይሉ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተልእኮ ለማስፈፀም እየሰራ በመሆኑ ከተመዋን ለማውደም እና ህዝቡን ለማበሳቆል መምጣቱን ገልፀው ቡድኑ የጋራ ጠላት በመሆኑ ሁሉም የጋራ አስተሳሰብ ይዞ ማውገዝ እንዳለበት አስገንዝበው ውድመት ለደረሰባቸው የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የስራ ቦታ ስለተመቻቸ ሰራተኞች ወደ ስራ መግባት አለባችሁም ብለዋል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ/ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top