የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ “በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ ከፓርቲ አባላት ሴቶች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

በመደረኩ ላይ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሀላፊ ወ/ሮ ቤተልሄም ክበቤ “በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል ርእሰ ጉዳይ ሰነድ አቅርበዋል፡፡ ሴቶች በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አንስተው ሴቶች የተሳተፉበት የትኛውም ተግባር ውጤታማ መሆኑን እና በተለያዩ ተግባራት ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውን ገልፀው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ሀገር መምራት ከጀመረ ወዲህ በርካታ ሴቶች የአመራርነት ሚና እንደተሰጣቸውም ጠቅሰው በሌሎችም ዘርፎች ተሳትፏቸውን ለማሳደግና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ተናግረው የሰላም እጦቱ በሴቶች ላይ ሰፊ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ሰላምን ለማምጣት ሴቶች መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበው መጭው ምርጫ በአግባቡ እንዲካሄድም ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙ ሴቶችም በሰጡት ሀሳብ በዘርፈ ብዙ ተግባራት ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውን እና አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀው ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ሰላምን ለማምጣት ሴቶች የድርሻችን አስተዋጽኦ ማበርከት አለብን ብለዋል፡፡
እንደ ከተማ አስተዳደር የሴቶችን ኦኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት ተይዞ መሰራት እንዳለበትም ተናግረው በአሁኑ ጊዜ በሀገር ደረጃ የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተሻለ መሆኑን እና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንስተው ሀገራዊዩ ምርጭ በጥሩ መንገድ እንዲካሄድ ለማድረግ መስራት አለብንም ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ያየሽ ድረስ እንደገለጹት አንድ ሀገር ትበልጽግ ከተባለች እና ሴቶች ያልተሳተፉበት የትኛውም ተግባር ውጤታማ ስለማይሆን ሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፏቸውን አጠናክረው ማስቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበው መጭው ምርጫ የተሳካ እንዲሆን ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
የሰላም እጦቱ በሴቶች ህጻናትና በሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ በርካታ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ሴቶች ሰላምን ለማምጣት መስራት እንዳለባቸው እና በጽናት መቆም እንደሚገባ አስገንዝበው ሴቶች ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ መስራት አለባቸውም ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ውባለም ታረቀኘ እንደተናገሩት ሴቶች ለሀገረ መንግስት ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው መሆኑን አንስተው ሴቶች የተሳተፉበት ማንኛውም ተግባር ውጤታማ በመሆኑ እያደረጉት ያለውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማስቀጠል እንዳለባቸው ጠቁመው ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግም ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
ሰላምን ለማረጋገጥም ሴቶች ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ እና ተግባራትን በተደራጀ መንገድ መፈፀም እንደሚያስፈልግ ተናግረው መጭው ሀገራዊ ምርጫ በጥሩ ሁኔታ እንዲካሄድም ሴቶች በትኩረት ይዘው ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበው እርስ በእርሳችን መተጋገዝና መደጋገፍ አለብንም ብለዋል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን የካቲት 02 ቀን 2018 ዓ/ም
