ከመሬት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚገባ ተመላከተ፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያውን ግማሽ አመት እቅድ አፈጻፀም ግምገማ መድረክ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ በመምሪያው የበጀትና እቅድ ዝግጅት ባለሙያ አቶ እሸቱ ተካ በተያዘው በጀት አመት ስድስት ወራት ውስጥ የተከናዎኑትን ተግባራት እቅድ አፈጻፀም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
በገጠር መሬት አስተዳደር፣ በከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥ፣ በቅየሳና ካርታ ዝግጅት፣ በካሳ ግመታና ትክ አሰጣጥ፣ በከተማ መሬት ዝግጅትና መልሶ ማልማት፣ በፋይል ማደራጀትና አጠቃቀም፣ በዘርፈ ብዙ ተግባራት፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና በሌሎችም ዘርፎች የተሰሩትን ስራዎች አመላክተዋል፡፡
የፓርቲ ተግባራት እና የለውጥ ስራዎች በአግባቡ እንዲፈፀሙ ጥረት መደረጉን አንስተው በየዘርፉ የሚከናዎኑትን ተግባራት በተሻለ መንገድ ለማከናዎን በትኩረት ተይዞ መሰራቱን ጠቁመው በቀጣይ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል እና ክፍተቶችን መሙላት አለብንም ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተሳተፉ አካላትም በሰጡት ሀሳብ ተግባሮቻቸውን በአግባቡ ለመፈፀም በትጋት ሲሰሩ መቆየታቸውን እና በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀው ስራዎችን በሚፈለገው መንገድ ለማከናዎን ያልተሟሉ መደቦችን በሰው ሀይል መሸፈን እና ግብአትን በበቂ ሁኔታ ማቅረብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ለአሰራር የማይመቹ ነገሮችን ማስተካል እንደሚገባ እና ስራዎችን በጥሩ መንገድ ለመስራት ሁሉም በባለቤትነት ይዞ መስራት እንዳለበትም አንስተው ተቋሙ ገቢ የሚያመነጭ እንደ መሆኑ መጠን በየክፍለ ከተማው የገቢ ሰብሳቢ ባለሙያ እንዲኖር ማደረግ እንደሚያስፈልግም ጠቁመው ስራዎቻችን ውጤታማ ለማድረግ ተቀናጅተን መስራት አለብንም ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር መሬት መምሪያ ሀላፊ አቶ ንጉሴ አሉበል እንደገለጹት በግማሽ አመቱ በርካታ ተግባራት መከናዎናቸውን እና ትልልቅ ስራዎችም መሰራታቸውን ጠቅሰው ተግባሮቻችን በሚፈለገው አግባብ ለመፈፀም በትኩረት ይዘን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
እንደ ተቋም የሚሰሩትን ስራዎች በተገቢው ሁኔታ ለመስራት ጥረት ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበው ከአጋር አካላት ጋር የሚሰሩትን ደግሞ ተቀራርቦ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ልንፈጽም ያቀድናቸውን ተግባራት በአግባቡ ለመፈፀም ሁላችንም በባለቤትነት ይዘን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ቄስ መልካሙ ላቀው እንደተናገሩት መሬት መምሪያው ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ በመሆኑ እና ዘርፈ ብዙ ተግባራት የሚከናዎኑበት በመሆኑ ለከተማ አስተዳደሩ የጀርባ አጥንት እንደሆን አንስተው ስራዎችን በአግባቡ ለመፈፀም ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ከመሬት ጋር ተያይዞ የሚነሱትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት እና ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠትም በትኩረት ይዞ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበው ተግባራትን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመፈፀም በቅንጅትና በትብብር መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ጥር 27 ቀን 2018 ዓ/ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top