የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር በግብርና ዘርፉ ለአርሶ አደሩ የብድር አገልግሎት ለማቅረብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የብድር ውል ስምምነት ተፈራርሟል።
በተካሄደው ስምምነት ላይም የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደሴ መኮንን እንደገለጹት ግብርናውን ለማዘመንና የአርሶ አደሩን ህይወት ለመቀየር የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ለማሟላት የብድር ስምምነቱ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡


የግብርና ዘርፎችን ከአበዳሪ ተቋማት ጋር ማስተሳሰር ተገቢ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ለአርሶ አደሩ የብድር ውል ትስስር መፍጠሩ ይበል የሚያሰኝ መሆኑንም አንስተው ከሌሎቹም ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረታቦር ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ አዱኛው አማረ እንደተናገሩት ባንኩ ባዘጋጀው የብድር ውል ዘመናዊ ግብርናን እውን ለማድረግ፣ አርሶ አደሩን የግብርና ግብአቶች ተጠቃሚ ለማድረግ እና የኑሮ ደረጃውን ለማሻሻል አበክረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
በመጨረሻም የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ፣ የመሬት መምሪያ እና የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት መምሪያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የብድር ውል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ጥር 15 ቀን 2018 ዓ/ም
