ከተማ አስተዳደሩ እንደ ከተማ አጋጥሞ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ሰላምን ለማጽናት እና የከተማውን ሰላም ለማረጋገጥ ሲሉ መስዋዕትነት የተቀበሉና የቆሰሉ የጸጥታ አካላትን እና ቤተሰቦችን አበረታቷል።


የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ መምሪያ ሀላፊ አቶ ብሩክ አለምነው እንዳሉት ታሪካዊ ከተማቸውን ሰላሟ እንዲከበር ህዝቧም በሰላም ወጥቶ እንዲገባ እኔ መስዋዕት ልሁን ብለው ዋጋ የከፈሉና የቆሰሉ የጸጥታ አካላት ክብር ይገባቸዋል የከተማችን ህዝብና ከተማ አስተዳደሩም ሁሌም ለእነሱ ክብር አለው ብለዋል።አጀንዳችን የህዝባችንና የከተማችን ሰላም ማረጋገጥና የልማት ፍላጎቱ እንዲሟላ መስራት ነው ያሉት ሃላፊው መንግስት ህዝብንና ሀገርን ያስቀደሙ የጸጥታ አካላትና ቤተሰቦችን ማበረታታቱ በመልካም የሚታይና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል።
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን እንደተናገሩት እንደ ከተማ ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር ለመቀልበስና አሁን ላለንበት ሰላም ለመድረስ የጸጥታ አካሉ የማይተካ የህይወት መስዋዕትነት ከፍሏል ብለዋል።በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ የጸጥታ አካሉ የከተማችን ሰላም የተሟላ እንዲሆን አሁንም ያለ እረፍት እየደከመ እንደሆነ በመግለጽ መስዋዕትነት ለተቀበሉ የጸጥታ ቤተሰቦችና ለቆሰሉ የጸጥታ አካላት ልዩ ክብር አለን እውቅናም እንሰጣለን ብለዋል።
በፕሮግራሙ መስዋዕትነት ለተቀበሉ የጸጥታ አካላት የሻማ ማብራት ስነ ስርአት ተከናውኗል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ጥር 16 ቀን 2018 ዓ/ም
