የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ ስርአቱን በጠበቀና በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል!

ደብረታቦር ከተማ የጥምቀት በዓልን ጨምሮ በወርሃ ጥር በአጅባር ሜዳ ሌሎች በርካታ ሁነቶችም ይስተናገዳሉ።በዓላቶች በድምቀት እንዲሁም በሀይማኖታዊ ስርአት እንዲከበሩ ለማድረግ በየደረጃው በመንግስት አካላት እና በሀይማኖት ተቋማት በኩል ዝግጅቶች ሲደረጉ ቆይቷል።
የሀገረ ስብከቱ አባቶች እና የከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ ተቋማት ሃላፊዎችም በዓሉ በድምቀት እንዲሁም ሰላማዊ ሁኖ እንዲጠናቀቅ በጋራ መሰራት ስለሚገባቸው ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል ።
ደብረታቦር ከተማ በአሁኑ ወቅት ፍጹም ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚደረግባት ከተማ በመሆኗ በከተማው የሚከበሩ ክብረ በዓላትን ከየትኛውም የአለም ክፍል የሚገኝና በቦታው ማክበር የሚፈልግ አካል መጥቶ ማክበር እንደሚችልም በውይይቱ ተነስቷል።
በከተማው በልዩ ሁኔታ በፈረስ ጉግስና በሽምጥ ግልቢያ የሚደምቀውን ጥር 25 የሚከበረውን የቅዱስ መርቆሬዎስ ክብረ በዓል በአጅባር ሜዳ ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ ስርአቱን በጠበቀ መልኩ እንደሚካሄድና በርካቶች በጉጉት የሚጠብቁት እንደሆነም ነው የተጠቀሰው።
በአጠቃላይ በወርሃ ጥር የሚከበሩ ክብረ በዓላት ለከተማው የቱሪዝም ምንጭ እንዲሆኑ ሁሉም ለሰላሙ ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት እንዳለበትም ተመላክቷል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ጥር 08 ቀን 2018 ዓ/ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top