ነጋዴዎች በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ያለ ቅጣት የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን እንዲያሳድሱ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አሳሰበ።

በከተመዋ በተለያዩ የንግድ ስራዎች ላይ የተሰማሩ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ያለ ቅጣት የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን እንዲያሳድሱ መምሪያው አሳሰቧል።

በንግድና ምዝገባ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት  ነጋዴዎች የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን ያለ ቅጣት የማሳደሻ ጊዜ ከሀምሌ 01 እስከ ታህሳስ 30 ባሉት ተከታታይ 6 ወራት ብቻ እንደሆነ በግልጽ ተደንግጓል።

በዚህ መሰረት በርካታ የከተማችን ነጋዴዎች የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን በወቅቱ በማደስ ስራቸውን በአግባቡ እየከወኑ ሲሆን በሌላ በኩል በተደጋጋሚ ግንዛቤና ቅስቀሳ ቢፈጠርም ጊዜ አለን በሚልና መሰል ምክንያቶች እስካሁን የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን ያላደሱ የከተማችን ነጋዴዎች እንዳሉ መምሪያው አረጋግጧል።

በመሆኑም በየትኛውም የንግድ ዘርፍ የንግድ ስራ ፈቃድ አውጥታችሁ እየሰራችሁ ያላችሁ ነጋዴዎች የንግድ ስራ ፈቃዳችሁን በአስቸኳይ በማሳደስ ተገቢ ካልሆነ እንግልትና ቅጣት ትድኑ ዘንድ መምሪያው እያሳሰብ በወቅቱ ባልታደሰ ፈቃድ ከጥር 01/2018 . ጀምሮ ተቋሙ እርምጃ በመውሰድ ፈቃዱ ለጥር ወር ብቻ ከማሳደሻ ውጭ 2500 ብር እየተቀጡ የሚያሳድሱ መሆኑን እየገለጽን በተለያየ ምክንያት ፈቃድ አውጥታችሁ ሲስተም ላይ የተመዘገባችሁ ነጋዴዎች ፈቃዳችሁን በወቅቱ የማታሳድሱ ወይም የማትሰሩበትን ፈቃድ የማትመልሱ ከሆነ ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት የማትችሉ መሆኑን መምሪያው ያሳስባል።

በወረፋና በሲስተም ምክንያት የሚፈጠሩ መጓተቶችን እንዲሁም የቀረውን አጭር ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ነጋዴዎችን ከቅጣት ለማዳን ታህሳስ 25 እና 26/2018 . ቅዳሜና እሁድን ጭምር አገልግሎት የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።

በመሆኑም ከዚህ ቀደም የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን ያላሳደሱ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የተመቻቸላቸውን እድል ተጠቅመው የንግድ ፍቃዳቸውን እንዲያሳድሱ መምሪያው መልእክት አስተላልፏል፡፡

 

   ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 21 ቀን 2018 .

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top