መነሻውን ባህርዳር አድርጎ ወደ ሰሜን ወሎ በመጓጓዝ ላይ የነበረ የጦር መሳሪያ በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር በተቀናጀ የጸጥታ መዋቅሩ ስራ መያዙን የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
በመምሪያው የወንጀል ምርመራ ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር መሳፍንት አባይ እንዳሉት ከብሄራዊ መረጃ አገልግሎት ጋር በመቀናጀት በተሰራው የጸጥታ ስራ መነሻውን ባህርዳር አድርጎ ከመደበኛ መንገድ ውጭ ከሃሙሲት ማህደረ ማርያም አድርጎ ወደ ሰሜን ወሎ ሲጓዝ የነበረ ታርጋ ቁጥር አ.ማ 17638 በሆነ አባዱላ በመጓጓዝ ላይ የነበረ አንድ ብሬን እና አንድ ስናይፐር የጦር መሳሪያ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በከተማ አስተዳደሩ አባረጋይ ላይ ባለው የኬላ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል፡፡

ሀገርን የማፍረስና የህዝብን ሰላምና ጸጥታ የማናጋት ተግባራት የሚሰሩ የውስጥና የውጭ ጠላቶች በመተባበር የሚፈጽሙት ቢሆንም በብሄራዊ መረጃና በከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ መዋቅር የተቀናጀ ስራ የጥፋት ተልዕኳቸውን በተከታታይ ማክሸፍ መቻሉንም አንስተዋል።
ህገወጥ ድርጊት ትልቅ ጉዳት ያለው በመሆኑ ያነሱት ኮማንደር መሳፍንት አባይ ድርጊቱን ለመከላከል አጎራባች ወረዳዎችና ዞኖች ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበው ማህበረሰቡ ህገወጥ ድርጊትን ለማስቆም ከጸጥታ ሃይሉ ጋር ተጋግዞ ሊሰራ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 09 ቀን 2018 ዓ.ም
