በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ለብልጽግና ፓርቲ አባላት መንግስት ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

“በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ለብልጽግና ፓርቲ አባላት መንግስት ሰራተኞች ለሁለት ቀናት የተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል፡፡
 
በግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ በገጠር ትራንስፎርሜሽን፣ በከተማ ትራንስፎርሜሽን፣ በቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰጥ የነበረው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቋል፡፡
በተያያዘም ስልጠና ሲወስዱ የነበሩት የከተማ አስተዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ አባላት መንግስት ሰራተኞች በከተመዋ በከፍተኛ በጀት እየተሰሩ ያሉትን የተለያዩ ፕሮጀክቶች እና አምራች ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በዚህም በመሰራት ላይ የሚገኙትን ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት፣ የገበያ ማእከል፣ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ወይቭላ ካምፓስን የጎበኙ ሲሆን በማምረት ላይ የሚገኙትን የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችንም ጎብኝተዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደሴ መኮንን እና የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ደበበ አክሎግ ተገኝተው መንግስት ሰራተኞችን አስጎብኝተዋል፡፡
በስልጠናው እና በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉ የፓርቲው አባላት መንግስት ሰራተኞችም በሰጡት ሀሳብ በስልጠናው ከተማችን ክልላችን እና ሀገራችን ወደ ጥሩ ደረጃ የሚያሸጋግሩ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ መገንዘባቸውን ገልፀው እያጋጠሙን ያሉትን ችግሮች ለመሻገር አንድ ሁነን በቁርጠኝነት መስራት አለብን ብለዋል፡፡
በሰላምና ፀጥታ ችግር ውስጥ ተሁኖ በከተመዋ እየተሰሩ ያሉት የልማት ስራዎች ይበል የሚያሰኙ መሆናቸውን እና አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ገልፀው የባህል ማእከሉ ግንባታ እንዲጠናቀቅ እና የአየር መንገድ በቅርቡ አገልግሎት መስጠቱን እንዲቀጥል ማድረግ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ታህሳስ 08 ቀን 2018 ዓ/ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top