በደብረታቦር ከተማ የቀጣይ 25 አመታት መዋቅራዊ ፕላን ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

የአብክመ ፕላን ኢንስቲትዩት በሰራው የከተመዋ መዋቅራዊ ፕላን ላይ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ ነዋሪዎች፣ ከከተማ አስተዳደሩ የስራ ሀላፊዎች፣ ከቡድን መሪዎች፣ ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች እና ከምሁራን ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ ላይ የአብክመ ፕላን ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች እንደገለጹት የተሰራው የደብረታቦር ከተማ የቀጣይ 25 አመታት መዋቅራዊ ፕላን የከተመዋን ዘላቂ ልማትና እድገት በሚያመጣ መንገድ የተዘጋጀ መሆኑን አንስተው ከተሰራው መዋቅራዊ ፕላን ጋር ተያይዞ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያቀረቡ ሲሆን በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ፣ በአረንጓዴ ልማት እና በሌሎችም ዘርፎች ያሉትን እንቅስቃሴዎች እና በቀጣይ መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች አመላክተዋል፡፡
በመዋቅራዊ ፕላኑ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የአየር መንገድ፣ ዘመናዊ ስታዲየም፣ የወጣቶች መዝናኛ፣ የህንጻ ግንባታዎች እና ሌሎችም ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች መካተታቸውን ጠቅሰው በከተመዋ በርካታ ምቹ ሁኔታዎች ያሉ በመሆናቸው ለዘላቂ ልማትና እድገት ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙ አካላትም በሰጡት ሀሳብ የክልሉ ፕላን ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች የሰሩት የከተመዋ መዋቅራዊ ፕላን የሚደነቅ መሆኑን ገልፀው ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተቋቁመው ፕላኑን በመስራታቸው አመስግነው ቢስተካከሉ ያሏቸውን ጉዳዮች አቅርበዋል፡፡
የተሰራው መዋቅራዊ ፕላን ለከተመዋ ዘላቂ ልማትና እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን እና ለአካባቢው ከተሞች እድገትም ጥሩ እድልን እንደሚፈጥር ገልፀው የተሰራው ፕላን በአጭር ጊዜ ወደ ተግባር እንዲገባ መደረግ አለበትም ብለዋል፡፡
በመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱት የተለያዩ ሀሳቦችም የአብክመ ፕላን ኢንስቲትዩት ባለሙያ አቶ ምናላቸው ታየ መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን እንደገለጹት የከተመዋ የቀጣይ 25 አመታት መዋቅራዊ ፕላን በጥሩ መንገድ የተሰራ መሆኑን አንስተው ፕላኑን ለሰሩት የክልሉ ፕላን ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበው መስተካከል አለባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች ጠቁመዋል፡፡
የተሰራው መዋቅራዊ ፕላን የከተመዋን የቀጣይ አመታት ልማትና እድገት ታሳቢ ባደረገ መልኩ መዘጋጀቱንም ገልፀው ነገሮችን አርቆ ማየትና ማሰብ እንደሚያስፈልግ እንዲሁም የሚሰሩትን ጉዳዮች ከፍ ባለና ዘመናዊ በሆነ መንገድ ለማስኬድ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደሴ መኮንን እንደተናገሩት መዋቅራዊ ፕላን ለአንድ ከተማ ልማትና እድገት ወሳኝ መሆኑን አንስተው የተሰራው የ25 አመት የከተመዋ መዋቅራዊ ፕላን የከተመዋን ቀጣይ እጣ ፈንታ የሚወስን መሆኑን ጠቁመው ፕላኑን የሰሩትን አካላትም አመስግነዋል፡፡
በመዋቅራዊ ፕላኑ የተካተቱት አብዛኛዎቹ ጉዳዮች ጥሩ መሆናቸውን እና ለከተመዋ እድገት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥሩም ገልፀው መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች እንዲስተካከሉ ለማድረግ እንደሚሰራም ተናግረው በፕላኑ ላይ ሁሉም መምከርና ሀሳብ መስጠት አለበትም ብለዋል፡፡
በተሰራው የደብረታቦር ከተማ የቀጣይ 25 አመታት መዋቅራዊ ፕላን የከተመዋ የቆዳ ስፋት 25 ሽህ ሄክታር መሬትን እንደሸፈነም ተገልጿል፡፡
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ህዳር 24 ቀን 2018 ዓ/ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top