“የፓርቲ መዋቅርን በማጠናከር ተግባራትን በመናበብ፣ በቅንጅት እና በማስተሳሰር መምራት የሞት የሽረት ጉዳይ ነው”

“የፓርቲ መዋቅርን በማጠናከር ተግባራትን በመናበብ፣ በቅንጅት እና በማስተሳሰር መምራት የሞት የሽረት ጉዳይ ነው”

ክቡር አቶ ይርጋ ሲሳይ

በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የተግባራት አፈፃፀም ግምገማ እና የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትኃላፊ ክቡር አቶ ይርጋ ሲሳይ ፣ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ዘሪሁን ፍቅሩ፣ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ፍስሃ ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የፖርቲ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ይርጋ ሲሳይ እንደተናገሩት፣ ከላይ እስከ ታች የሚገኘውን የፖርቲ መዋቅርን በማጠናከር ተግባራትን በመናበብ ፣ በቅንጅት እና በማስተሳሰር በውጤታማነት መምራት የሞት የሽረት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

የፓርቲው መዋቅር ሚናው ከፍ ያለ ነው ያሉት ኃላፊው፣ መዋቅሩ እንደአስኳል ሁኖ ሁሉንም ተግባራት የመምራት እና የማስተሳሰር ኃላፊነትን በማጠናከር የፖለቲካ ስራዎችን በላቀ ትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

በሁሉም ተግባራት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብም በሁሉም እርከኖች ግልጽ ውይይት እና መግባባት እንደሚጠይቅም ጨምረው ተናግረዋል።

Amhara Prosperity Party /APP/

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications

Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications

Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO

You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication

Website: https://www.amharacomm.gov.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top