
በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር በየደረጃው ከሚገኙ ጠቅላላ አመራሮች ጋር የሚመክር ወቅታዊ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር በየደረጃው ከሚገኘው ከጠቅላላ የፖለቲካና የጸጥታ አመራሮች ጋር በቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ ስለሚገባቸው ጉዳዮች የሚመክር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የፖለቲካና የጸጥታ አመራሩ እስካሁን እንደ ከተማ አስተዳደር የተሻለ ሰላምን ለማምጣትና የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን የነበረውን ሚና በተመለከተ በመድረኩ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
የፖለቲካና የጸጥታ አመራሩ የህዝብን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥና የልማት እንቅስቃሴዎችን በሚፈለገው አግባብ ለማስኬድ በቀጣይ መቶ ቀናት የክረምት ወራት የስራ እቅድ አውጥቶ እንደ ተቋም መስራት እንዳለበትም በመድረኩ ተነስቷል።
የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል በትኩረት እንዲሰራም በመደረኩ ተጠቅሷል።በቀጣይ ወቅቱ የክረምት ወቅት ስለሆነ የግብርና ስራዎችን በትኩረት ይዞ መስራት፣ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር፣የተጀመሩ የመሰረተ ልማቶችን በጥራትና በፍጥነት መስራት፣አርኪ የአገልግሎት አሰጣጥ ስራ መስራትና ጠቃሚና አሻጋሪ የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን መስራት እንደሚገባም ተጠቁሟል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ/ም
ተጨማሪ መረጃዎችን በሌሎች የሚዲያ አማራጮች ይመልከቱ!
ፌስ-ቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100064645364506
ቴሌግራም ቻናል ፡- https://t.me/dtcommunication
ትዊተር፡- https://twitter.com/debre_tabor_com
ዩቲዩብ፡- https://youtu.be/BktVrGvXms
